የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አመሰራረት

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት እ.ኤ.አ በ1976 በኢትዮጵያና በጀርመን መንግስት መካከል በተደረገው የትብብር ስምምነት መሠረት የእጽዋት ጀነቲክ ሀብት ማዕከል (A Plant Genetics Resource Center) በሚል ለመጀመሪያ ጊዜ ተቋቋመ፡፡ በመቀጠልም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. አፕሪል 5/1994 54ኛዋ ሀገር ሆና የዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ስምምነት ስትፈርም ይህንን ለማስፈፀም ይቻል ዘንድ በእጽዋት ላይ ብቻ ሲሰራ የቆየውን የእጽዋት ጀነቲክ ሀብት ማዕከል (PGRC/E) የእንስሳትና የደቂቅ አካላት እንዲጨምር ተደርጎ ሕይወታዊ ሀብት ጥበቃና ምርምር ኢንስቲትዩት (IBCR) በሚል በአዲስ መልክ ተቋቋመ፡፡ እ.ኤ.አ በ2004 በአዲስ መልክ ጥብቃ ላይ እንዲያተኩር ታስቦ የብዝሀ ሕይወት ጥበቃ ኢንስቲትዩት (IBC) በሚል ተቋቋመ፡፡

ሕይወታዊ ሀብትና ተያያዥ ነባር እውቀት እንዲሁም እነዚህን አቅፎ የያዘውን ስርዓተ-ምህዳር የመጠበቅ፣ የማልማትና በዘላቂነት ጥቅም ላይ እንዲውል ሁኔታዎችን ማመቻቸት በሚል አቅጣጫ ተይዞ ስራዎች እንየተከናወኑ ነው፡፡

በሀገራችን የአየር ንብረት ለውጥ መከሰት፣ ድርቅና በረሀማነት መስፋፋት፣ የህዝቡን ቁጥር ከልማት እድገር ጋር ባልተመጣጠነ ሁኔታ መጨመር እንዲሁም ብዝሀ ሕይወት ጥበቃን ያላገናዘቡ ልማቶችንና ሀብቶችን ዘላቂነት ባለው መንገድ ለመጠቀም ካለመቻል የተነሳ ይህ ሀብት መልሶ ሊተካ የማይችልበት ሁኔታና እየተመናመነ የሚገኘውን የሀገሪቱን ብዝሀ ሕይወት በሚገባ የመቃኘት፣ የመሰብሰብ፣ ጠብቆ በዘላቂነት የማቆየትና ተረባርቦ ቀጣይነት ባለው መልኩ ጥቅም ላይ የማዋል ስራ ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶ እየተተገበረ ይገኛል፡፡

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት በጀነቲክ ሀብትና ተያያዥ የማህበረሰብ እውቀት እንዲሁም የሚኖሩበትን ስርዓተ-ምህዳር ተለያይነቱን በጠበቀ ሁኔታ ለመጠበቅና በዘላቂነት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ ማህበረሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ይሰራል፡፡

በተጨማሪም ከሀብቱ የሚገኘውን ጥቅም ፍትሀዊ በሆነ መልኩ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር የምርምርና ፍቃድ የመስጠት ሀላፊነትም ተሰጥቶታል፡፡

ኢንስቲትዩቱ የሀገሪቱን ብዝሀ ሕይወት ሀብትና ተያያዥ የማህበረሰብ እውቀቶች ጥበቃ፣ ዘለቄታዊ አጠቃቀም እና ፍትሀዊና ሚዛናዊ ጥቅም ተጋሪነትን የሚመለከቱ የፖሊሲና የህግ ሀሳቦችን በማመንጨትና ሲፈቀዱም ስራ ላይ ማዋልና መዋላቸውን የመከታተል እንዲሁም በሀገሪቷ የሚገኘውን የእጽዋት፣ የእንስሳትና ደቂቅ አካላት ተለያይነትንና ስርጭትን በመቃኘትና በማሰስ የሀገሪቷን ብዝሀ ሕይወት ሀብት መጠንና ባህሪያትን መለየትና መገምገም እንዲሁም የሚገኙበትን ሁኔታ በየጊዜው የመከታተል ሀላፊነት የተሰጠው ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አደረጃጀት

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አደረጃጀት

  1. ዋና ዳይሬክተር /ቤት
  2. ማክትል ዋና ዳይሬክተር

ተጠሪነታቸው ለዋና ዳይሬክተሩ ሆኖ በሰው ኃይል የሚደራጁ
1.1 ኤክስክዩቲቭ ሴክሬታሪ
1.2 ሥርዓተ ጾታ ኦፊሰር
1.3 የሥነ-ምግባርና ጸረ ሙስና መኮንን
1.4 የአመራር ሥራዓት ለውጥ ትግበራ ቡድን መሪ
1.5 የአመራር ሥርዓት ለውጥ  ትግበራ ኤክስፐርት

  1. ሰባት አጋዥ የሥራ ሂደቶች ማለትም

2.1 የውስጥ ኦዲት ዳየሬክቶሬት
2.2 የፕላንና ፕሮግራም ዳየሬክቶሬት
2.3 የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳየሬክቶሬት
2.4 የግዥ፣ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳየሬክቶሬት
2.5 የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳየሬክቶሬት
2.6. የኢንፎርሜሽንና ኮሙኑኬሽን ቴክኖሎጂ ዳየሬክቶሬት
2.7. የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ዳየሬክቶሬት

  1. አምስት የምርምር የሥራ ሂደቶች ማለትም

3.1 የደንና የግጦሽ መሬት ዕፅዋት ብዝሀ ሕይወት ዳየሬክቶሬት
3.2 የአዝርዕትና ሆርቲካልቸር ብዝሀ ሕይወት ዳየሬክቶሬት
3.3 የደቂቅ አካላት ብዝሀ ሕይወት ዳየሬክቶሬት
3.4 የእንስሳት ብዝሀ ሕይወት ዳየሬክቶሬት
3.5 የጄኔቲክ ሀብት አርክቦትና ጥቅም ተጋሪነት ዳየሬክቶሬት