የብዝሀ ሕይወት ናሙና ማስገቢያ ማመልከቻ
በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 291/2005 አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 13 መሠረት የብዝሀ ሕይወት ናሙና ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚፈልግ አመልካች ማመልከቻው ከዚህ በታች ያሉትን መስፈቶች ማካተት ይኖርበታል፡-
- ጠቅላላ መረጃ
- የአመልካቹ ተቋም ስምና አድራሻ፣
- የተቋቋመበት ሰነድ (ተቋሙ የተቋቋበት ሕግ ወይም የምዝገባ ሠርተፊኬት፣ እንዲሁም ተቋሙ በኢትዮጵያ የሚገኝ በይነ-መንግሥታዊ ተቋም ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሠራ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ያደረገው ስምምነት ኮፒ)፣
- ዝርዝር መረጃ
- የብዝሀ ሕይወት ናሙና ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚቀርብ ሕጋዊ የማመልከቻ ደብዳቤ፣
- የምርምር ወይም የጥናት ንድፈ ኃሳብ፣
- የምርምሩ ዓላማ፣ የሚጠበቅ ውጤት፣
- የጀነቲክ ሀብቱ ናሙና ዓይነትና መጠን (በግራም፣ በኪሎ ግራም፣ በቁጥር…)፣
- ለምርምሩ ወይም ለጥናቱ ኃላፊነት የሚወስደው ተቋም
- ወደሀገር ውስጥ እንዲገባ የተጠየቀው ብዝሀ ሕይወት ናሙና ሳይንሳዊና አካባቢያዊ ስያሜ
- ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ የተጠየቀው የብዝሀ ሕይወት ናሙና መጠን (በቁጥር)
- የብዝሀ ሕይወት ናሙናው የተላከበት / የመጣበት ሀገር
- የብዝሀ ሕይወት ናሙናው ተያያዥ መረጃ (Passport data and pedigree)
- የብዝሀ ሕይወት ናሙናው ከበሽታና ከተባይ ነፃ መሆኑን የሚያስረዳ ሰነድ/ ሠርተፊኬት፣
- የብዝሀ ሕይወት ናሙናው ከልውጠ ሕያው ነፃ መሆኑን የሚያስረዳ ሰነድ/ ሠርተፊኬት፣
- የጀነቲክ ቁስ ማስገቢያ ሥምምነት ሰነድ (ከኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ድረ-ገፅ http://www.ebi.gov.et/gm-access/gm/ላይ የሚገኝ)
- በ አምስት ዋና ቅጂዎች የተዘጋጀ የጀነቲክ ቁስ ማስገቢያ ስምምነት ሰነድ (በብዝሀ ሕይወት አስገቢው ተቋም በአግባቡ ተሞልቶ የተፈረመበትና ሕጋዊ ማኅተም የተደረገበት)፣
- መረጃዎቹ በአግባቡ የተሟሉለት (የምርምር ዓላማ፣ የሚጠበቅ ውጤት፣ የጀነቲክ ሀብት ናሙና ዓይነትና መጠን፣ የብዝሀ ሕይወት ሀብቱ ሳይንሳዊ ስያሜ፣ የብዝሀ ሕይወት ሀብቱ የመጣበት አገር)፣