የጀነቲክ ሀብት አሰሳ ፈቃድ ማመልከቻ
በጀነቲክ ሀብትና የማኅበረሰብ ዕውቀት አርክቦት የማኅበረሰብ መብቶች አዋጅ ቁ.482/1998 አንቀጽ 23 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ጀነቲክ ሀብት አሰሳ ለማድረግ የሚፈልግ አመልካች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መሥፈርቶች አሟልቶ ሊያቀርብ ይገባል፡፡
- ጠቅላላ መረጃ
- የአመልካቹ ወይም የድርጅቱ ስም (የተፈጥሮ ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል)፣
- የተመዘገበ አድራሻ እና የተቋቋመበት ሰነድ (የሰነዱ ኮፒ ይያያዛል)፣
- በታቀደው አሰሳ ውስጥ የሚሳተፉት ሰዎች ስም ዝርዝርና ሙያ (ካሪኩለም ቪቴ ይያያዛል)፣
- የአሰሳ ማመልከቻውን በሚመለከት ግንኙነት ማድረግ የሚቻለው ሰው ስም፣ አድራሻ እና በድርጅቱ ውስጥ ያለው ኃላፊነት፣
- ዝርዝር የአሰሳ መረጃ
- በጀነቲክ ሀብት ላይ አሰሳ ለማድረግ የሚቀርብ ሕጋዊ ማመልከቻ ደብዳቤ፣
- የአሰሳው ዓላማ በዝርዝር፣
- የሚታሰሰው የጀነቲክ ሀብት ዓይነት፣
- አሰሳው የሚካሄድበት አካባቢ፣
- አሰሳው ሊካሄድ የታቀደበት የጊዜ ሠሌዳ፣
- የአሰሳ ማመልከቻው ላይ በበቂ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ለመስጠት ሊረዳ የሚችል ማንኛውም መረጃ፣
- ቃለ መኃላና ፊርማ
- ኃላፊነት ያለው ሰው ስም፣
- ኃላፊነቱ (በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠውን አካል በመወከል ከሆነ)፣
- ፊርማና ቀን