የጀነቲክ ሀብት ከጂን ባንክ / ከመስክ ለማርከብ የሚቀርብ የጀነቲክ ሀብት አርክቦት ማመልከቻ (በሀገር ውስጥ ጥናትና ምርምር ለማካሄድ)

ከኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ጂን ባንክ ወይም ከመስክ ጀነቲክ ሀብቶችን ለማርከብ (ለመውሰድና ለመጠቀም) የሚፈልግ አንድ አርካቢ (ተመራማሪ) የሚከተሉትን መሠረታዊ መስፈርቶች ያካተተ ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

 1. ጠቅላላ መረጃ
 • የአመልካቹ ተቋም እና አድራሻ፣
 • የተቋቋመበት ሰነድ (ተቋሙ የተቋቋበት ሕግ ወይም የምዝገባ ሠርተፊኬት፣ እንዲሁም ተቋሙ በኢትዮጵያ የሚገኝ በይነ-መንግሥታዊ ተቋም ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሠራ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ያደረገው ስምምነት ኮፒ)፣
 1. ዝርዝር መረጃ
 • የጀነቲክ ሀብት ናሙና ከኢንስቲትዩቱ ጂን ባንክ / ከመስክ ለማርከብ የሚቀርብ ሕጋዊ የማመልከቻ ደብዳቤ፣ ደብዳቤው በመ/ቤቱ የበላይ ሓላፊ የተፈረመ ፣ የመዝገብ ቁጥር ያለው እና ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት
 • የተመራማሪውና የጀነቲክ ሀብቱ የሚወስደው ስም በደብዳቤው መገለጽ አለበት
 • የተመራማሪው / አጥኚው አግባብነት ያለው መታወቂያ፣
 • በማኅተምና ፊርማ የተረጋገጠ የምርምር / የጥናት ንድፈ ኃሳብ ሁለት ኮፒ
 • የምርምሩ ዓላማ፣ የሚጠበቅ ውጤት፣ የጀነቲክ ሀብቱ ናሙና ዓይነትና መጠን (በግራም፣ በኪሎ ግራም፣ በቁጥር፣… ወዘተ)፣
 • ለማርከብ የተፈለገው የጀነቲክ ሀብት ሳይንሳዊ ሥያሜ (ቢቻል እስከ ዝርያ ደረጃ ድረስ የተለየ)፣
 • የጀነቲክ ሀብቱ የሚገኝበት ቦታ፣
 • ጀነቲክ ሀብቱ ሊውል የታሰበበት ጠቀሜታ በዝርዝር
 • ምርምሩ የሚፈጀው ጊዜና ከምርምሩ የሚጠበቀው ውጤት
 • አመልካቹ / ተመራማሪው ከጂን ባንክ ፎርም በመውሰድ ከጂን ባንክ የሚወሰደውን ጀነቲክ ሀብት ጠቅሶ መፈረም ይኖርበታል፡፡
 1. ከመስክ የሚሰበሰቡ የጀነቲክ ሀብት ናሙናዎች
 • የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት እና የምርምር ተቋማት፣ ከመስክ የጀነቲክ ሀብትና የማህበረሰብ ዕውቀትን ለመሰብሰብ ከኢንስቲትዩቱ ፈቃድ መጠየቅ አያስፈልጋቸውም፣
 • የጀነቲክ ሀብቱንና ተያያዥ የማህበረሰብ ዕውቀቱን ለሦስተኛ ወገን ለማስተላለፍ ወይም ከሀገር ለማስወጣት ከፈለጉ ግን ከኢንስቲትዩቱ ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፣

አርክቦት ማመልከቻ ፎርም

የጀነቲክ ሀብት ከጂን ባንክ ለማርከብ የሚቀርብ ማመልከቻ

የአርክቦት አገልግሎትን በተመለከተ እባክዎን የአስተያየት ይስጡ ፡፡