ለንግድ ዓላማ የጀነቲክ ሀብት አርክቦት ማመልከቻ

በጀነቲክ ሀብትና የማኅበረሰብ ዕውቀት አርክቦት የማኅበረሰብ መብቶች አዋጅ ቁ.482/1998 አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 1 እና በደንብ ቁ.169/2001 አባሪ I መሠረት ጀነቲክ ሀብትን ለንግድ ዓላማ ለማርከብ የሚፈልግ አመልካች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን አሟልቶ ሊያቀርብ ይገባል፡፡

 1. ጠቅላላ መረጃ (የተፈጥሮ / የሕግ ሰው)
 • የአመልካች ተቋሙ ስም እና የተመዘገበ አድራሻ፣
 • የትምህርት መረጃ/ሙያ፣
 • የማቋቋሚያ ሰነድ፣
 • ለማመልከቻው ትክክለኛነት ተጠያቂ የሚሆነው ሰው፣ ኃላፊነት፣ ሙሉ አድራሻ እና ፊርማ
 1. ዝርዝር የአርክቦት መረጃ (የገንዘብ ነክ እና የቴክኒክ መረጃ)
 • የጀነቲክ ሀብት ለማርከብ የሚቀርብ ሕጋዊ ማመልከቻ ደብዳቤ፣
 • የአርክቦት ፕሮጀክቱ በጀት፣
 • የአርክቦት ፕሮጀክቱን የደገፉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ዝርዝር፣
 • የጀነቲክ ሀብቱ ሳይንሳዊ መረጃ፣ ለማርከብ የተፈለገው የጀነቲክ ሀብት ሳይንሳዊ ስያሜ (ቢቻል እስከ ዝርያ ደረጃ ድረስ የተለየ)
 • የጀነቲክ ሀብቱ የሚሰጠው/ወደፊት ሊሰጥ የሚችለው ጠቀሜታ፣
 • የጀነቲክ ሀብቱ ሊሰበሰብ የታሰበበት አካባቢ (የሚታወቅ ከሆነ)
 • የጀነቲክ ሀብቱ ሊገኝ የሚችልባቸው ሌሎች አካባቢዎች ዝርዝር (የሚታወቅ ከሆነ)፣
 • ለማርከብ የተፈለገው ጀነቲክ ሀብት መግለጫ (ሕብረ ህዋስ፣ ዘር፣ ቅጠል፣…ወዘተ)፣
 • የሚሰበሰበው ጀነቲክ ሀብት መጠን (በግራም፣ በኪሎግራም፣ በቁጥር…ወዘተ)፣
 • ከጀነቲክ ሀብቱ ጋር ተያይዞ የሚገኝ የማህበረሰብ ዕውቀት፣
 • አርክቦት የሚፈፀምበት የጀነቲክ ሀብት የሚገኘው በኢዘቦታ ከሆነ፣ የጀነቲክ ሀብቱን ይዞ የሚገኘው ተቋም ማንነት፣
 • ለማርከብ የተፈለገውን የጀነቲክ ሀብት የሚያቀርበው ሰው ማንነት፣
 • የጀነቲክ ሀብቱ የሚገኘው በመሰብሰብ ከሆነ የሚሰበሰብበት ስልት፣
 • በጀነቲክ ሀብት አሰባሰብ ላይ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችና ተቋሞች የሚሳተፉ ከሆነ እንማን እንደሆኑ፣
 • የጀነቲክ ሀብት አሰባሰብ የሚጀመርበትና የሚጠናቀቅበት የጊዜ ሠሌዳ፣
 • የአርክቦት አመልካች የጀነቲክ ሀብቱን ለመለየትና ለመሰብሰብ ድጋፍ የሚፈልግ ከሆነ የሚፈልገው የድጋፍ ዓይነት፣
 • ጀነቲክ ሀብቱ ሊውል የታሰበበት ጠቀሜታ፣
 • የምርምሩ ዓይነትና ጥልቀት፣ ጥቅም ላይ የሚውለው የባለሙያና የመሣሪያ ዓይነት፣
 • ከምርምሩ የሚጠበቀው ውጤትና ምርምሩ የሚወስደው ጊዜ (በግምት)፣
 • ምርምሩና የማልማት ሥራው የሚካሄዱባቸው ቦታዎች፣
 • ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች በምርምሩ ውስጥ የሚሳተፉ ከሆነ የሚሳተፉበት ሁኔታ እና የተሳትፏቸው ጥልቀት፣
 • በምርምሩ ውስጥ ሊሳተፉ እና ሂደቱን ሊቆጣጠሩ የሚችሉ ኢትዮጵያውያን ተቋማት እነማን እንደሆኑ (ሊታወቅ የሚችል ከሆነ)፣
 • የጀነቲክ ሀብቱ መጀመሪያ እና በቀጣይነት ሊወሰድ የሚችልባቸው ቦታዎች፣
 • የአርክቦት አመልካቹ የውጭ ሀገር ዜጋ ከሆነ፣ ከሀገሩ መንግሥት ሥልጣን ያለው አካል አመልካቹ የአርክቦት ፈቃድ ቢሰጠው የሚኖርበትን የአርክቦት ግዴታዎች በዚያ ሀገር የሚያስከብርና የሚያስፈጽም መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣
 • ለሀገሪቷ ወይም ለሚመለከተው የአካባቢ ማህበረሰብ ያስገኛል ተብሎ የታሰበው ወይም ሊያስገኝ የሚችለው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ቴክኖሎጂያዊ፣ ሳይንሳዊ፣ አካባቢያዊ ወይም ሌሎች ማናቸውም ጥቅሞች
 • የአርክቦት ማመልከቻው ላይ በበቂ ግንዛቤ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት ሊረዳ ይችላል በማለት አመልካቹ የሚገምተው ሌላ ማናቸውንም መረጃ ሊያካትት ይገባል፡፡

ለንግድ ዓላማ የጀነቲክ ሀብት አርክቦት ማመልከቻ


የአርክቦት አገልግሎትን በተመለከተ እባክዎን  የአስተያየት ይስጡ ፡፡