በለማዳ እንስሳት ብዝሀ ህይወት ጥበቃና ዘለቄታዊ አጠቃቀም ላይ አወደጥናት ተካሄደ፡፡

በኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የእንሰሳት ብዝሀ ሕይወት ዳይሬክቶሬት ከአፍሪካ ሕብረት የእንሰሳት ሀብት ማዕከል ጋር በመተባበር ለተለያዩ የባለድርሻ አካለት በሀገሪቱ የለማዳ እንሰሳት አጠባበቅ እና ዘለቄታዊ አጠቃቀም ላይ ጥቅምት 26 እና 27 እንዲሁም ጥቅምት 29 እና 30 በአዳማ ከተማ ድሬ ኢንተርናሽናል ሆቴል ለተለያዩ ታዳሚዎች አውደ ጥናት አካሄደ፡፡

አውደ ጥናቱን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ እንደገለፁት ኢትዮጵያ በመልካምድር አቀማመጥ፣በተለያየ አየርንብረት፣በበርካታ ባህሎች እና በብዝሀሕይወት ሀብቷ እጅግ የበለፀገች መሆኗ የተረጋገጠ ነው ብለዋል፡፡

በቋንቋ ረገድ  ከሰማንያ በላይ የሆኑ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሀገር ከመሆኗም በሻገር ይህ የቋንቋና የባህል ተለያይነት  ለብዝሀሕይወት ሀብታችን በተለይም ለእንስሳት ብዝሀሕይወት ተለያይነት ናስብጥር፣ ጥበቃናዘለቄታዊ አጠቃቀም የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጓል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ኢተዮጵያ በእንስሳት ሀብቷ በተለይም በግብርናው ዘርፍ  ከፍተኛ  ጠቀሜታ ባላቸው የለማዳ  እንስሳት ተለያይነት ማእከልነቷ ትታወቃለች በማለት ገልፀዋል፡፡

አቶ አብረሀም አሰፋ የእንሰሳት ብዝሀ ሕይወት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ባቀረቡት ፅሁፍ ስለ ሀገሪቷ የእንሰሳት ብዝሀ ሕይወት ተለያይነት፤ የእንሰሳት ብዝሀ ሕይወት የመመናመን አደጋና ይህንን ለመቅረፍ በርካታ ስራዎች የተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በዚሁ መሰረት የሀገራችን ለማዳ እንሰሳት የባህሪ ትንተና፤ የዘቦታና የኢዘቦታና ዘለቄታዊ አተቃቀም ላይ ሰፊ ገለፃ ሰተዋል፡፡

አቶ አበበ ሀይሉ ለማዳ የእንሰሳት ብዝሀ ሕይወት ሀብት ጥበቃን አስመልክቶ የታቀደውን ቤሔራዊ እንሰሳት ስትራቴጂክ እና የድርጊት መርሀ ግብርን አስመልክቶ ሰፊ ማብራርያ ያቀረሙ ሲሆን ሌሎችም የዳሬክተሬቱ ተመራማሪዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በለማዳ እንስሳት ያሉ ትቅሞችንና ተግዳሮቶችን የሚያመላክቱ የምርምር ውጤቶች ለታዳሚው አቅርበዋል፡፡

በአጠቃላይ በአውደ ጥናቱ ለማዳ እንሰሳትን በተመለከተ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት የተላለፉ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ በቤተሰብም ሆነ በሀገር ደረጃ የእንስሳት ሀብቱ ለዘመናት የግብርናና የቱሪዝም

ክፍለ ኢኮኖሚው መሰረት ሆኖ መቆየቱን በሀገር ደረጃ ከአጠቃላይ ምርቱ 25 ፐርሰንት ከግብርናው ዘርፍ ደግሞ አንድ ሶስተኛውን እንዴዘ፤ የእንስሳት ሀብት ዘርፉ ለሀገራችን ግብርናና የስበት ኃይል የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከታከለበት ለሀገራዊ ምርቱ ያለው አስተዋጽኦ አስከ 45 ፐርሰንት እንደሚደርስ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱ ተገልፅዋል፡፡ይሁን እንጂ የእንስሳት ብዝሀ ሕይወት ዘርፉ የተለያዩ   የመመናመን አደጋዎች እነዳሉበት የተገለፀ ሲሆን እነዚህም ከፍተኛ የማዳቀል አገልግሎት፣ ዝንደርቢ፣ ድርቅ፣ ግጭትና ጠንካራ  የእንስሳት ሀብት መለየት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ስራዎች ያለመተግበር ዋናዋናዎቹ መሆኖን ተጠቅሷል፡፡ ስለሆነም የእንስሳት ብዝሀሕይወት ሀብት ምርምር፣ ጥበቃ፣አጠቃቀምና ልማቱ ሊጠናና በአግባቡ ሊተገበር እንደሚገባ በአፅዕኖት ተገፅዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *