በትምህርት ቤቶች ክበባት ላይ በጋራ ስለመሥራትን መለከታል፣

በፌዴራል እና በክልል ደረጃ በሚገኙ ውስን ትምህርት ቤቶች ላይ የአካባቢ ጥበቃ ክበባትና የብዝሀ ሕይወት ክበባት ተቋቁመው የአካባቢ ፅዳትና የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ነገግን ይህ ሥራ ከፌዴራል ተቋማት በተቀናጀ መልኩ የአካባቢና የብዝሀ ሕይወት ጉዳይን ያካተተ የት/ቤት ማንዋል ተዘጋጅቶ መተግበሩ ውጤታማ ከማድረጉ ባሻገር በሁለቱም ተቋማት ዘንድ የሚኖረውን ተደጋጋሚ  ወጪና ሥራ ድካምን ስለሚቀንስ  የሚኒስቴር መ/ቤቱ የሕብረተሰብ ግንዛቤ ማሳደግያ እና ማጎልበቻ ዳይሬክቶሬት ከኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩቱ ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን የሥራ ሂደት ዳይሬክቶሬት ጋር በጋራ ቢሰራ በነገው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ የሚደረገው የግንዛቤ መፍጠር ሥራ ፍሬያማ ያደርጋል ብለን እናምናለን፡፡በመሆኑም ለዚሁ ዓለማ ስኬት የሚኒስቴር መ/ቤቱ የሕብረተሰብ ግንዛቤ ማሳደግያ እና ማጎልበቻ ዳይሬክቶሬት ከኢኒስቲትዩቱ ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን የሥራ ሂደት ዳይሬክቶሬት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንዲቻል አቅጣጫ እንዲሰጥበት በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡  

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *