የኢትዮጵያ ብዝሀሕይወት ኢንስቲትዩት ከጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የጂኦፖርታል አስተዳደር ሥልጠና ሰጠ

ሥልጠናውን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ብዝሀሕይወት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈለቀ  ወልደየስ ሥልጠናው ኢንስቲትዩቱ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችል ነው፡፡ ኢንሲቲትዩቱ የሚያከናውናቸውን ብዝሀሕይወትን የመጠበቅ ፣ በዘላቂነት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማድረግና ከብዝሀሕይወት ሀብት ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በየደረጃው እየተከናወነ ያለውን ስራ ጥራት፣ተአማኒነትና ጊዜ ቆጣቢነት ለማረጋገጥ  የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡በተጨማሪም በተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ለምሳሌ፡ በግብርናና በውሀና መሰኖ  ኢነርጂ ሚ/ር መ/ቤቶች …ወዘተ ተበታኖ የሚገኝውን የብዝሀሕይወት ሀብት መረጃ  በማሰባሰብና በማቀናጀት መጠቀም ይቻል ዘንድ የዚህ ዓይነቱ ሥልጠና በጣም ጠቃሚና አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ብዝሀሕይወት ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አንተነህ  ለገሰ   በበኩላቸው ይህ ሥልጠና  የኢንስቲትዩቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ  ባለሙያዎች ቀድሞ የነበረውንና ከ18 ዓመት በላይ ያስቆጠረውን የተቋሙን  ድረ-ገጽ ለማዘመን፣አካታችና ተደራሽ ለማድረግ የምናደርገውን ጥረት የሚያግዝ ነው ፡፡ኢንስቲትዩቱ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ሀላፊነት ለመወጣት ፤ የተመረጡ መረጃዎችን ለሕብረተሰቡ ለማድረስ እና የሁሉንም  ዒላማ ፈጻሚ  ዳይሬክተሬቶችን መረጃ በሚያካትት  መልኩ ስራችንን ለማከናወን የሚያስችል የሥራ ላይ ሥልጠና ነው ብለዋል፡፡

እንደ አቶ አንተነህ  ገለጻ ሥልጠናው እንደ  ኤርትራና  ሶማሌ  ካሉ ጎረቤት  አገራት ጋር ተቀላሎ  የሚገኝውን  የጂኦስፓሻል መረጃ አጥርቶ ለመያዝና  የሚሰበሰበውን  የጂኦስፓሻል መረጃ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆንለማስቻል የሚያግዝ ነው፡፡ በተጨማሪም የኢንስቲትዩት ሠራተኞች ይህንን ሥልጠና በመጠቀም 2 ቀን ይፈጅባቸው የነበረውን ስራ በሰከንድ ውስጥ ከ60 እስከ 70 በመቶ  ከዳታው ውስጥ ለቅመው በማውጣትና በማዳበር ብቻ መጠቀም  የሚያስችል አቅም ይፈጥርላቸዋል ብለዋል፡፡

የሥልጠናው አጋር የሆነው በኢትዮጵያ  የዓለም  አቀፉ ጥቅም ተጋሪነትና አርክቦት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ጌትነት አባተ   የአርክቦትና ጥቅም ተጋሪነት ዳታ ቢዝን ለማልማት፣መረጃ ፈላጊዎች የሚፈልጉትን መረጃ ኦን ላይን እንያገኙ ለማድረግና የኢትዮጵያ ብዝሀሕይወት ኢንስቲትዩትን ድረ -ገጽን ከCBD ABS CH  ጋር ለማገናኝትና ለማልማት ነው ይህ ሥልጠና የተዘጋጀው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ብዝሀሕይወት ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት  የጂአይኤስ ቡድን መሪና  የሥልጠናው  አስተባባሪ አቶ ታሪኩ ገዳ ሥልጠናው  የዘርፉን   ዓለም አቀፍዊ ተሞክሮ ለአገራችን ተስማሚና ተጠቃሚ  እንዲሁም ማንኛውም ሰው በቀላሉ ሊጠቀምበት በሚችል መልኩ የጂአይኤስ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡አቶ ታሪኩ  አክለውም ለተመራማሪዎችም ባሉበት ሆነው መረጃን መጠቀም የሚችሉበት ሥርዓት ለመዘርጋትም ያሥችላል ብለዋል፡፡ወደ መረጃ  ቋት የሚገቡ መረጃዎች የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ፣አስተማማኝና ተዓማኒ የሆኑ እና መረጃውን  የሚሰበስበው  አካል ስራውን በግልጸንነትና ተጠያቂነት እንዲያከናውን የሚያስችለው መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

የሥልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሥልጠናው  ጠቃሚ፣ግልጽና  አሳታፊ እና ከጂኦ ፖርታል ጋር ያስተዋወቀን ነው ብለዋል፡፡በዳታ ቢዝ በኩል ያለብንን ችግር የሚፈታ ፣የማፒንግ  ባዮዳይቨርሲቲ እና የአርክቦትና ጥቅም ተጋሪነት ችግር ለመፍታት የሚያስችልና በቀጣይ ሊያሠራ የሚችል ሀሳብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ሁሉን አቀፍ የመረጃ ቋት በማዘጋጀት ለኅብረተሰቡ ተደራሽ የማድረግ ስራ በቅርቡ የሚጀመር ይሆናል ይህንን ለማድረግ የሚያሥችል መግባባትም ከጂኦስፓሻል  ኢንስቲትዩት  ጋር ፈጥረናል ብለዋል፡፡

ስልጠናውን በንግግር የዘጉት የኢትዮጵያ ብዝሀሕይወት ኢንስቲትዩት  ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማሪዮ ይህ ስልጠና የተቋማችን የመረጃ ስርዓት ለማጠናከርና ለማዘመን ጥሩ ጅማሮ በመሆኑ ሂደቱ ቀጣይነት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *