በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከቴ.ቢ.ኤል.ሲ ኃ..የተ .የግ.ማሕ ጋር የተቀናጀ የፋይናንስ መረጃ አስተዳደር ሥርዓትን( IFMIS) በተመለከተ ተወያዩ

በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከቴ.ቢ.ኤል.ሲ ኃ..የተ .የግ.ማሕ ጋር የተቀናጀ የፋይናንስ መረጃ አስተዳደር ሥርዓትን( IFMIS) በተመለከተ ተወያዩ

በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የመሰብሰቢያ አዳራሽ መጋቢት 5 ቀን 2011ዓ.ም ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከቴ.ቢ.ኤል.ሲ ኃ..የተ .የግ.ማሕ ጋር የተደረገውን የውይይት የመሩት የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ ኢንስቲትዩቱ ተግባሪ ተቋም መሆኑ ጥሩ ነው፡፡የኢንስትቲዩታችን የአይ.ሲ.ቲ ክፍል ጠንካራ በመሆኑ የአሰራር ስርዓቱን ቀላልና ለአጠቃቀም ምቹ በማድረግ ሁሉም ሰራተኞች በቀላሉ ሊጠቀሙበት የሚያስችል አቅም እንዲፈጥር ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ አጠቃላይ የአሰራር ስርዓቱን ሰራተኞች ተግባራዊ በሚያደርጉበት ጊዜ ወደ ስህተት እንዳይገቡ የሚከላከል መመሪያ እና ደንብ ሊቀመጥ የሚገባ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የሥልጠናው አደረጃጀት ጥሩ እንደነበር ገልጸው የገንዘብ ሚኒስቴር የድጋፍና የክትትል ባለሙያዎች ያደረጉልን ድጋፍና ክትትል ጥሩ ስለነበር ምስጋናችን ከልብ ነው ብለዋል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉ የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሠራተኞች በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የተቀናጀ የፋይናንስ መረጃ አስተዳደር ሥርዓት( IFMIS)ተግባራዊ ለማድረግ የሚያሥችል ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩት አቶ ዳንኤል ቸርነትና አቶ ጥሩነህ ለገሰ የተባሉ ከገንዘብ ሚንስቴተር የመጡ የክትትከልና የድጋፍ ባለሙያወች ሲሰጡ የነበረው ድጋፍ እጅግ ጥሩ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ እ.ኤ.አ ማርች 2018 ጀምሮ ወደ ተቀናጀ የፋይናንስ መረጃ አስተዳደር ሥርዓትን( IFMIS) መተግበር የጀመረው የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ካጋጠሙት ችግሮች መካከል ለሥልጠናው የተሰጠው ጊዜ ማነስ፣የጸሀፊዎችና የፋይናንስ ባለሙያዎች ሥራ ሲለቁ ሌላ በተቀናጀ የፋይናንስ መረጃ አስተዳደር ሥርዓት( IFMIS)የሠለጠነ ባለሙያ ስለሌለ ክፍተት መፈጠሩ ፣ደሞዝና ስራ ማስኬጂያ በሚገባው ልክ ማግኝት አለመቻሉ፣ሥልጠናው በየግል ኮምፒዩተር ላይ ብቻ እንዲሆን መደረጉ፣የአሰራር ስርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራው አናሳ መሆኑ፣የአሰራር ስርዓቱን ተግባራዊ ለማረግ የግብዓት ችግሮ መኖር፣ከፔሪድ መዘጋትና መከፈት ጋር በተያያዘ ደሞዝ አይከፈልም መባሉ ፣ሥልጠናው የሥራ ላይ ስልጠና እንዲሆን አለመደረጉ፣ሥልጠናው ከተሰጠ በኋላ ወደ ተግባር ሳይገባ ለሁለት ወራት መቆየቱ፣አንድ ሰው በአንድ አይነት ሥልጠኛ ብቻ እንዲሰለጥ መደረጉ ፣ዋናው የመረጃ ቋት ላይ ያለው የዕቃዎች ዝርዝር የምርምር ዕቃዎችን ያማከለ አለመሆኑ፣ከአስተዳደር ችግር ጋር በተያያዘ ፈጣን ምላሽ የመሥጠት ችግር መኖሩ፣የመናበብ ችግር መኖሩ፣በየደረጃው ያሉ ፈፃሚ አካላት መካከል ክፍተቶች መኖራቸው፣ከካፒታል በጀት ዝውውርጋር በተያያዘ የበጀት መቀነስ ችግር መኖሩ፣ከሪፖርት ጋር ተያይዞ የወረቀት አሠራርን ማስቀረት አለመቻሉ፣በአሰራር ስርዓቱ ዙሪያ የጠራ ግንዘቤ አለመፈጠሩ እና የዋናው የመረጃ ቋት ዝግጅት አሳታፊ አለመሆኑ ተነስተዋል ፡፡ ለተነሱት አስተያየቶችና ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የቴ.ቢ.ኤል.ሲ ኃ..የተ .የግ.ማሕ ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ለገሰና በገንዘብ ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ባለሙያ አቶ ምህረት ታከለ በሰጡት ምላሽ ለአዲስ ሠራተኞች ፣ለነባር ሠራተኞች ተከታታይ ሥልጠናዎችንና የአቅም ክፍተት ላለባቸው ባለሙያዎች ሥልጠናዎች የመስጠቱ ሁኔታ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ የአሰራር ስርዓቱን ከማስረጽ አንጻር የገንዘብ ሚኒስቴር ሰራተኞች መቆየት ካለባቸው ጊዜ በላይ ቆይተው የድጋፍና የክትትል ስራ ማከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከጸሀፊዎች በተጨማሪ ባለሙያዎችም ሥልጠናውን ወስደው መስራት ይችላሉ ፤አንድ ሰው ሁለትና ሶስት ዓይነት ሥልጠናዎችን በመውሰድ የትምህርት ሚኒስቴርን ተሞክሮ መነሻ በማድረግ መስራት ይችላል፡፡ እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ የአሰራር ሥርዓቱ የውክልና አስራርን የሚያስተናግድበት አግባብ አለው አጽዳቂ አካል ለጊዜው ባይኖር ሌላ ሰው እሱን ወክሎ ሊያጽቅ ይችላል፡፡ ለሥልጠናው የተሰጠው ጊዜም በቂ ነው ነገርግን ሥልጠናው በፍጥነት የገባቸው ሠራተኞች በኢንስቲትዩቱ ቦታ ተዘጋጅቶላቸው ሌሎችን ማሠልጠን ቢችሉ፣ሰራተኞች አቅማቸውን በሥልጠናና በራሳቸው ጥረት መገንባት ቢችሉ መልካም እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ የተነሱት ችግሮች በአብዛኛው የሚያያዙት ከቴክኒካል ሳይሆን ከአስተዳደራዊ ችግሮች ጋር በመሆኑ በየደረጃው ካሉ አስፈጻሚ አካላት ጋር በመነጋገገር የሚፈቱ መሆናቸው አመልክተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *