የብሔራዊ ስነምህዳር የዳሰሳ ጥናት ሰነድ አዘጋጆች የውይይት መድረክ ተካሄደ

የብሄራዊ ስነምህዳር የዳሰሳ ጥናት ሰነድ ዝግጅት ጸሀፊያንና አርታኤያን የውይይት መድረክ መጋቢት 6 ቀን 2011ዓ.ም በአዳማ ከተማ ቶኔ ዶት ሆቴል ላይ ሲደረግ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የደንና ግጦሽ መሬት እጽዋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና የብሄራዊ ስነምህዳር የዳሰሳ ጥናት ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር ዲቢሳ ለሚሳ ይህ የውይይት መድረክ የሥነምህዳር ዳሰሳ ቅኝት በሚደረግበት ጊዜ የሚያጋጥሙ መልካም ነገሮችን የምንዳስስበትና ከተግዳሮቶች የምንማርበት ነው፡፡ የዳሰሳ ጥናቱ እረጅም ጉዞ የተጓዝንበት ፣በርካታ ተግባራትን ያከናወንበትና ወደፊትም ሰፋ ያለ ሥራ መስራት ስለሚጠበቅብን ግንኙነታችን ፣ትብብራችንና አብሮነታችንን የምናጠናክርበት በመሆኑ ወደፊትም እንዲህ አይነት መድረክ ፈጥሮ የመወያየት ሂደቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዩጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ በበኩላቸው ይህንን የውይይት መድረክ ያዘጋጀነው ካደረግነው ቅኝትና ከሰበሰብነው ግብረ መልስ በመነሳት ነው፡፡ ሳይስንና ፖሊሲዎችን በማገናኝት ዘላቂ የሕይወታዊ ሀብት ጥበቃ ለማምጣት የሚያስችል ልዩ ቁርጠኝነት የሚያሥፈልግ በመሆኑ ነው፡፡ በዓለም ደረጃ ሶስት አገራት ብቻ ናቸው ይህንን ሥራ ሲሰሩ የነበረው ፡፡ እኛ ዘግይተን ወደ ስራው የገባን ቢሆንም በአጭር ጊዜ ውስጥ የሠራነውን ሥራ በማየት የዓለም አቀፉ ተቋም ፕሮጀክት በእኛ ላይ እምነት አሳድሯል ፡፡ ይህንን አመኔታና ኃላፊነት ለመወጣትና ከፍተት እንዳይታይ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል፡፡ ሁላችንም በሥራው ላይ እየተሳተፍን ያለን አካላት በተደራራቢ ሥራዎች ጫና ምክንያት በእኩል ፍጥነት ላይ ባንሆንም በቀጣይ ለሥራው ልዩ ትኩረት በመስጠት ተቀራራቢ ደረጃ ላይ ለመምጣት የምንችልበት ዕድል ሰፊ ነው ብለዋል፡፡
ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ የደንና ጫካ ስነምህዳርን በተመለከተ ፤ፕሮፌሰር አዱኛ ቶሌራ የመኖሪያ ስነምህዳርን በተመለከተ ፤ ፕሮፌሰር ጤና አላምረው እርጥበታማና ውሃማ ስነምህዳርን በተመለከተ፣ ፕሮፌሰር ስለሺ ኒሞሚሳ የተራራማ አካላት ስነምህዳርን በተመለከተ ፤ፕሮፌሰር ዘመዴ አስፋው የእርሻማ ስነምህዳራት ስነምህዳርን በተመለከተ እና ዶ/ር መኩሪያ አርጋው የብሔራዊ ስነምህዳር ዳሰሳ እድገት የሚያስከትለውን ውጤት በተመለከተ ጥናታቸው የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጓል ፡፡
ጥናታዊ ሪፖርተቹን መሠረት አድርጎ በተደረገው ውይይት ከተነሱ ሀሳቦች መካከል የመረጃ እጥረት ፣ጥራት ያለው መረጃ በበቂ ሁኔታ አለመኖር ፣በብዝሀ ሕይወት ዙሪያ የክትትልና የቁጥጥር ሥራው ከረጅም ጊዜ በፊት የተጀመረ አለመሆኑ ከመረጃ ምንጭ አንጻር እንደ ችግር ተነስቷል ፡፡ ከቴለፎንና ከኢሜይል ውጪ በአካል ተገናኝቶ ሥራዎች የደረሱበትን ሁኔታ መገምገም ላይ ውስንነቶች እንዳሉ ተገልጿል፡፡ ከናሙና አወሳሰድ ጋርም ተያይዞ በርከት ካሉ ቦታዎች ናሙናዎችን የመውሰድ ችግር፡፡ሪፖርት አቀራረቡ ሁሉንም ያማከለ አለመሆንና ሪፖርት ስታይሊንግ ፎር ማት አለመኖር፡፡ የሚዘጋጀው ሰነድ ገጹን መወሰን ቢቻል፣ የሀሳቦች መደጋገም ይታያል ይሕ የአንባቢን ፣የጽሁፉ ፍሰት ላይም ቢታሰብበት፣ የቅንጅት ወይም የመናበብ ችግር፣የውህደት ችግር ወይም አንዱን ሀሳብ ከሌላው ሀሳብ ጋር አሰናስሎ የሚሂድ ችግር፣ በሁሉም የሰነዱ ምዕራፎች ላይ የማጠቃለያ መልዕክት እንዲገባ አለመደረጉ፣በሚሉና በሌሎች በርካታ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደረጓል፡፡
ለተነሱት አስተያቶችና ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የተሰባሰበው የሰው ሀይል ጥሩ ነው፡፡ይህን የሠው ሀይል ለማሰባሰብ ከአስር ቀን በላይ ፈጅቶብናል ፡፡ የሪፖርት ፎርማትን ተከትሎ መስራት አስፈላጊ ነው፡፡ከልክ በላይ እንዳይሰፋ በሚል የተነሳው ሀሳብም ጥሩ ተቀባይነት ያለው ሀሳብ ነው፡፡ ተመሳሳይ ሀሳቦች በተለያየ ርዕስ ይመጣሉ ነገር ግን እርስ በእርስ እንዳይጣረሱ ጥንቃቄ መደረግ አለበት ፡፡ ፣ጽሁፉ ፍሰቱን የተከተለ፣የተቀናጀ፣ የተሰናሰለ እንዲሆን ይደረጋል፣ር በሁሉም የሰነዱ ምእራፎች ላይ የማጠቃለያ መልእክት እንዲገባ ይደረጋል፣የግንኙነት ጊዜ በቴሌፎንና በኢሜይል ከማድረግ በተጨማሪ ከቡድኑ አባላት መደበኛ የሆነ ጥያቄ ሲቀርብ የግንኙነት ሂደቱን ማመቻቸት ይቻላል፡፡ የመስክ ሥራዎች እጅግ በጣም ወሳኝ ናቸው፡፡ ከመስክ የሚመጡ መረጃዎች ሥራችንን የሚያጠናክሩ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የደንና ግጦሽ መሬት እጽዋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና የብሄራዊ ስነምህዳር የዳሰሳ ጥናት ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር ዲቢሳ ለሚሳ በበኩላቸው መረጃ ከማሰባሰብ ጋር ተያይዞ የትራንስፖርት ችግር ካጋጠመ መኪና ከመከራየት ጀምሮ ያጋጠመውን ችግር ለመቀነስ ሰፊ ጥረት ለማድረግ ዝግጁነት መኖሩን ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *