ለዓለም አቀፉ የብዝሀ ሕይወት ስምምነት የሚቀርብ የስድስተኛው አገራዊ ሪፖርት ፀደቀ

ለዓለም አቀፉ የብዝሀ ሕይወት ስምምነት የሚቀርበው የ6ተኛው አገራዊ ሪፖርት ረቂቅ የግምገማ መድረክ በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል የሀገራዊ ዝግጅት የስትሪንግ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ሀገራዊ ሪፖርት ብሔራዊ የብዝሀ ህይወት ስትራቴጂና የድርጊት መርሃ ግብር የትግበራ ደረጃ ሪፖርት ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማርዮ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የስብሰባው ዋና ዋና አጀንዳዎች ለዓለም አቅፍ የብዝሀ ሕይወት ስምምነት የሚቀርበውን የስድስተኛው አገራዊ ሪፖርት ረቂቅ ገምግሞ ማጽደቅ፣ ብሔራዊ የብዝሀ ሕይወት ስትራቴጂና የድርጊት መርሀ ግብር ትግበራ ወቅት ውስንነት በታየባቸው ጉዳዮች ላይ ተነጋግሮ ቀጣይ አቅጣጫ ማመልከትና በመጨረሻም የሚነሱ ተጨማሪ ሀሳቦች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ለስትሪንግ ኮሚቴው ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ስምምነት 54ተኛ ፈራሚ ሀገር እንደመሆኗ የሚቀርበው አገራዊ ሪፖርት መሆኑንና ከዚህ በፊት ለ5ኛጊዜም ሪፖርቱ እንደተደረገ ይህም ሪፖርት ዝግጅቱን የሚጠይቀዉ የዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ስምምነት አንቀጽ 26 ነዉ እንዲሁም ፈራሚ ሀገራትም በስምምነቱ የተቀበሉትን ግዴታዎች መፈፀም አለባቸዉ፡፡ በዚህ መሰረት ኢትዮጲያ NBSAP 2015-2020 (እኤአ) የትግበራ ደረጃ የሚመለከት የስድስተኛ ሀገራዊ ሪፖርት አዘጋጂታለች ሲሉ የኢትዮጵያ  ብዝሀ ሕይወት ስትራቴጂና የድርጊት መርሀ ግብር ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር ምስክር ተሰማ ገልፀዋል፡፡

በሪፖርት ዝግጅት ወቅትም በዋናነት ‹‹ይህንን ስትራቴጂና የድርጊት መርሀ ግብራችንን ካላሳካን የዘላቂ ግባችንን ልናሳካ አንችልም በሚል መንፈስ ለተሳካ አላማ እንረባረብ›› በሚል መልኩ ሪፖርቱ ሲዘጋጅ የነበር ሲሆን የተለያዩ የሚንስቴር መስራቤቶች በዝግጅቱ ላይ ተሳትፈውበታል፡፡ ዶ/ር ምስክር ተሰማ  አክለውም በሪፖርቱ ዝግጅት ጊዜ ያጋጠሙ ተግዳራቶችን በአገር አቀፍ ፣ በተቋምና በአለም አቀፍ ደረጃ በመከፋፈል እንደ የተሟላ የሰው ሀይል አለመኖር፣ የበጀት ችግር፣የመሪ ተግባሪ ተጠሪ ባለሙያ በየወቅቱ መቀያየር፣ አደረጃጀቱን የማስተካከል ችግር  መናበብ ችግር እና የመሳሰሉት ናቸዉ ፡፡

በዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ስምምነት ሴክረተሪያት በተላከዉ ፎርማት መሰረት የተዘጋጀዉ ይህ ሪፖርቱ በአምስት ግቦች፣ 18 ዒላማዎችና 58 ዋና ዋና ተግባራት ሥር የተሰሩ ተግባራት የገመገመ ሲሆን ሪፖርቱ በባለሞያዎች ቀርቧል ፡፡ የተሳተፉት የስትሪንግ ኮሚቴ አባላትም በቀረቡት ማብራሪያዎች ላይ ሀሳብና አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት፣ ከአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ ባዮዳይቨርሲቲ ፎረም፣ ከኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን፣ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምርት ሚኒስቴር እና ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኙ የስትሪንግ ኮሚቴ አባላት ስድስተኛው አገራዊ ሪፖርትን ረቂቅ በሙሉ ድምጽ አፅድቀዋል፡፡

አቶ ካህሳይ (ከዱር እንስሳት ባለስልጣን)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *