በሂደት ላይ ያሉ እና አዳዲስ የተቀረጹ የምርምር ፕሮጀክቶች ዓመታዊ ብሔራዊ የምርምር ግምገማ አውደ ጥናት ተካሄደ

በሂደት ላይ ያሉ እና አዳዲስ የተቀረጹ የምርምር ፕሮጀክቶች ዓመታዊ ብሔራዊ የምርምር ግምገማ አውደ ጥናት ተካሄደ

በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከየካቲት 27 እስከ የካቲት 29 ቀን 2011ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት የተደረገውን ኢንስቲትዩቱ በብዝሀ ህይወት ጥበቃ ላይ ከሚያከናውናቸው የምርምር ሥራዎች መካከል በሂደት ላይ ያሉ እና አዳዲስ የተቀረጹ የምርምር ፕሮጀክቶችን ዓመታዊ ብሔራዊ የምርምር ግምገማ አውደ ጥናት መድረክን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማሪዮ የብዝሀ ሕይወት ሀብታችንን በመጠበቅ፣በዘላቂነት ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግና ከብዝሀ ሕይወት ሀብታችን የሚገኝውን ሀብት በፍትሀዊነት ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ በዘርፉ የሚደረጉ የተለያዩ የምርምር ሥራዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው በዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን አጠናክሮ ለመቀጠል ኢንስቲትዩቱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የምርምር አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ውቢት ዳዊት በበኩላቸው የብዘሀ ህይወት ጥበቃና አጠቃቀም ዘላቂና በእዉቀት ላይ የተመሠረተ ለማድረግ በአዝእርትና ሆርቲካልቸር፣ በደንና ግጦሽ፣ በደቂቅ አካላት፣ በእንስሳት እንዲሁም በአርክቦትና ጥቅም ተጋሪነት ዘርፎች የሚካሔዱ የምርምሮች ሥራዎች ድርሻ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
በምርምር ዙሪያ ያጋጠሙ ችግሮች፤ የምርምር ፕሮጀክቶች አዋጭነት እና ፋይዳ ላይ በተደረገው ዓመታዊ ብሔራዊ የምርምር አውደ ጥናት ግምገማ መድረክ ላይ 78 የምርምር ፕሮጀክቶች ቀርበው የተገመገሙ ሲሆን ከቀረቡት ፕሮጀክቶች መካከልም 45 በሂደት ላይ ያሉ እና 33 አዳዲስ የተቀረጹ ናቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *